Episodios

  • የሚያዚያ 29 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    May 7 2025
    -የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸዉና ጥቅማጥቅሞች እንዲከበሩላቸዉ በየሚሰሩበት ተቋማት በመሠለፍ ጠየቁ።በተለያዩ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄያቸዉ ተገቢ መልስ ካላገኘ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚመቱ አስጠንቅቀዋል።---ሕንድና ፓኪስታን አዲስ የገጠሙትን ግጭት እንዲያቆሙ የተለያዩ መንግሥታት ጠየቁ።ሁለቱ ኑክሌር የታጠቁ ተጎራባች መንግስታት ግን አንዳቸዉ ሌላቸዉን ለማጥቃት እየተዛዛቱ ነዉ።-ፈረንሳይና ጀርመን ፍራንኮ-ጀርመን የተባለ የመከላከያና የፀጥታ የጋራ ምክር ቤት ለመመሥረት ተስማሙ።
    Más Menos
    12 m
  • የዓለም ዜና ፤ ሚazeያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ
    May 6 2025
    አርስተ ዜና፤--የክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት ፓርቲ መሪ ፍሪድሬሽ ሜርስ አዲሱ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆኑ። ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲህ 10ኛዉ የጀርመን ቻንስለር ሜርስ ቃለ-መሃላ ፈፅመዉ ሥልጣኑን በይፋ ተረክበዋል።--በአማራ ክልል ከመተማ ጎንደር ያለው መንገድ ከተዘጋ አንድ ወር በማስቆጠሩ በአካባቢው ነዋሪዎች የማህበራዊና ኢኮኒሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና ማሳደሩን ነዋሪዎች ተናገሩ።--ለሃገራት የሚሰጠዉ ሰብዓዊ እርዳታ መቀነስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እድገት እንዲቀዛቀዝ ምክንያት ሆኗል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
    Más Menos
    12 m
  • DW Amharic ሚያዝያ 27 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    May 5 2025
    የእስራኤል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ለሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገቡ። በአማራ ክልል ደሴ እና ወልድያ ከተሞች የአጭር ርቀት አሽከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሱዳን በተፈጸመ የጅምላ ፍጅት ተባባሪ ሆናለች በሚል የሱዳን መንግሥት ያቀረበውን ክስ የተመ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ። የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በጫማ ተመቱ። የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት ፣ ክርስቲያን ሶሻል ኅብረት እና ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ (SPD) ጥምር መንግሥት የመሠረቱበትን ሥምምነት ተፈራረሙ። እስራኤል ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመያዝ የሚያስችል ዕቅድ ማጽደቋን ባለሥልጣናት ተናገሩ።
    Más Menos
    12 m
  • የሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    May 4 2025
    *የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዛሬ እሁድ በፖርት ሱዳን ከተማ ላይ የድሮን ጥቃት መሰንዘሩን የሱዳን ብሔራዊ ጦር ቃል አቀባይ ተናገሩ። *የየመን ሁቲ አማጺያን በዓለም አቀፉ የቴል አቪቭ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ያነጣጠረ የሚሳኤል ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ እስራኤል ከፍተኛ የአፀፋ እርምጃ እንደምትወስድ ገለፀች። *የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምን ያህል የሀገሪቱን ህገ መንግሥት የማክበር ግዴታ እንዳለባቸው ርግጠኛ እንዳልሆኑ ተናገሩ። *ኢትዮጵያውያኑ ለሚ ብርሃኑ እና ብርቱካን ወልዴ በቼክ ሪፑብሊክ ዋና ከተማ ፕራግ ዛሬ የተካሄደውን የማራቶን ውድድር በየዘርፋቸው አሸነፉ
    Más Menos
    8 m
  • የሚያዝያ 25 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    May 3 2025
    የአስራ አራት ሀገራት ኤምባሲዎች “በኢትዮጵያ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ብርቱ ጫና ውስጥ ሆኖ መቀጠሉ” እንደሚያሳስባቸው ገለጹ። በደቡብ ሱዳን በድሮን ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 20 መቁሰላቸውን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን አስታወቀ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ድሮኖች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው የከሰላ ከተማ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ወታደራዊ የመረጃ ምንጮች ተናገሩ። ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ለሦስት ቀናት ተኩስ ለማቆም ላቀረቡት ምክረ-ሐሳብ ዩክሬን ግልጽ ምላሽ እንድትሰጥ ክሬምሊን ጠየቀ። በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያኑ ጽጌ ዱጉማ፣ በሪሁ አረጋዊ እና አብርሀም ስሜ አሸናፊ ሆኑ።
    Más Menos
    9 m
  • የዐርብ ሚያዝያ 24 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    10 m
  • የሚያዝያ 23 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    11 m
  • የሚያዚያ 22 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    Apr 30 2025
    -ኢትዮጵያ ዉስጥ መብታቸዉን ለማስከበር በሚጠይቁ ሠራተኞች ላይ አሠሪዎች የሚደርሱት ጫናና በደል እንዲቆም የሐገሪቱ የሠራተኛ ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ጠየቀ።---የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፀጥታ አስከባሪዎች ለሱዳን መከላከያ ጦር ሊላክ ነበረ ያሉትን በሚሊዮን የሚቆጠር ጥይት መያዛቸዉ ተነገረ።የሱዳን መከላከያ ጦር ግን የአቡዳቢን መግለጫ በሱዳን ሕዝብ ዓይን ዉስጥ አዋራ ለመሞጀር የተቃጣ ዉሸት በማለት አጣጥሎ ነቅፎታል።---የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሰዓዳ-የመን ዉስጥ ባደረሰዉ የአዉሮፕላን ጥቃት የአፍሪቃ ሥደተኞች የተጠለሉበትን ማቆያ ጣቢያ አወደመ።የየመን ባለሥልጣናት እንዳሉት በድብደባዉ 68 ሰዎች ተገድለዋል።
    Más Menos
    11 m
adbl_web_global_use_to_activate_webcro805_stickypopup