የዓለም ዜና Podcast Por DW arte de portada

የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

De: DW
Escúchala gratis

OFERTA POR TIEMPO LIMITADO | Obtén 3 meses por US$0.99 al mes

$14.95/mes despues- se aplican términos.
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።2026 DW Política y Gobierno
Episodios
  • የጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Jan 18 2026
    ግብፅ እና ሱዳን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ሀሳብ አወደሱ፤የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የከተራ በዓልን በድምቀት እያከበሩ ነው፤ኡጋንዳ የኢንተርኔት አገልግሎት በከፊል መስራት ጀመረ፤ በኢራን ፀረ መንግሥት ተቃውሞዎች እስከ 18,000 የሚደርሱ ሰዎች ሳይገደሉ አልቀረም፤የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ
    Más Menos
    10 m
  • የጥር 9 ቀን፤ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Jan 17 2026
    የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአባይ ውሃ ባለድርሻነት ለአንዴና ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኝ በሚል ግብጽ እና ኢትዮጵያን ዳግም ወደ ድርድር ለማስገባት አገራቸው አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ፡፡ የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራም የግብፁ ፕረዚደንት ዓብደልፋታሕ አልሲስን የጋዛ የሰለም ቦርድ አድርገው ማጨታቸውን ታውቋል።የ81 አመቱ የኡጋንዳ ፕረዚደንት ዩዌሪ ሙሰቨኒ ሐሙስ ዕለት በተካሄደም ምርጫ ማሸነፋቸውን የሐገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ይፋ አደረገ። ሩስያ ሌሊቱን ለዛሬ አጥቢያ በዩክሬይን ግዛት በፈጸመችው ጥቃት አንድ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋም ማውደሟን ናፍቶ-ጋዝ የተባለ የግል ኩባንያ አስታወቀ።
    Más Menos
    11 m
  • የጥር 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    Jan 16 2026
    • ከሑመራ ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች “ደሕንነታቸው ተጠብቆ በክብር፣ መረጃ ኖሯቸው እና በፈቃደኝነት” ወደ ቀያቸው መመለስ መጀመር አለበት የሚል አቋም አሜሪካ እንዳላት በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ተናገሩ። • በዩጋንዳ ትናንት ሐሙስ በተደረገው እና ዛሬ ውጤቱ ይፋ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተቀሰቀሰ ተቃዉሞ በትንሹ አስር ሰዎች ተገደሉ። • አዲሱን የጋዛ የሽግግር አስተዳደር ስራ የሚቆጣጠር ዓለማቀፍ ተቆጣጣሪ ቦርድ ማቋቋማቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናላድ ትራምፕ አስታወቁ። • በኢትዮጵያ የፊልምና የመዝናኛ ዘርፍ እውቁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
    Más Menos
    12 m
Todavía no hay opiniones