Episodios

  • በምርጫ ቦርድ እውቅናው የተሰረዘው ሕወሓት፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ያወጡትን መግለጫ ነቀፈ
    Jan 17 2026
    በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ሑመራ ከተማን ከጎበኙ በኋላ ያወጡት መግለጫ፤ በፕሪቶሪያ ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ፈራሚዎች መካከል አለ ያለውን "ሰፊ ​​ክፍተት ከማጥበብ ይልቅ የሚጎዳ ሂደትን የበለጠ ሊያባብስ እንደሚችል" ሕወሓት ባወጣው መግለጫ ገለልጿል።
    Más Menos
    4 m
  • የጥር 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    Jan 16 2026
    በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሑመራ ጉብኝት፤ በሲዳማ ዞን በደረሰ የመኪና አደጋ ሁለት ጥንዶችን ጨምሮ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፤ በኢትዮጵያ የተከሰተው ቀዝቃዛ የአየር ጸባይና ጉንፋን ፤ የአሜሪካ የስደተኝነት ቪዛ እገዳና የዝነኛው አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ህልፈት
    Más Menos
    27 m
  • በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የትናንቱ መግለጫ ምን ያመለክታል?
    Jan 16 2026
    በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ትናንት ባወጣው መግለጫ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ "በሑመራ ደማቅ አቀባበል" እንደተደረገላቸው የሚገልጽ ነው። አምባሳደሩ በስፍራው ያሉ ሰዎች "የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች በዐይኔ ተመልክቻለሁ" ብለዋል።
    Más Menos
    5 m
  • የጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    Jan 15 2026
    በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ስምንት ፓርቲዎች ሀገራዊ ምክክር በክልሉ እንዲካሄድ ለማገዝ ተስማምተዋል። በጋምቤላ ክልል በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት የአድማ ብተና እና የመደበኛ ፖሊስ አባላት የታጠቁትን የጦር መሣሪያ እንዲያስረክቡ የተሰጣቸው ትዕዛዝ ዛሬ ያበቃል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከዛሬ 11 ሰዓት በኋላ “የጦር መሣሪያ በእጁ የተገኘ እንደ ፀረ-ሠላም ተቆጥሮ” እርምጃ ሊወሰድበት እንደሚችል አስጠንቅቆ ነበር። በዛሬው ዜና መጽሔት ከሚቀርቡ ዘገባዎች መካከል ሁለቱ ይገኙበታል።
    Más Menos
    19 m
  • የረቡዕ ጥር 6 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    Jan 14 2026
    የዓለም ዜናን ተከትሎ፤ በሚቀርበው የዜና መጽሔት ጥንቅር በኤርትራው ፕረዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሰሞኑ ቃለምልልስ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች ያወዛገበው የአባገዳዎች ሽምግልና ሂደት የሶማሊያ ካቢኔ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን እና ትብብርን በሙሉ ማገዱን፣ የአውሮፓ ህብረትም እና አሜሪካ ለኢራን ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን፤ የሚያስቃኙ አራት ርዕሰ ጉዳዮች ተካተዋል።
    Más Menos
    20 m
  • የጥር 5 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    Jan 13 2026
    ፖለቲካ ድርጅቶች ቁጥርና ሀገር የሚገባው የፖለቲካ ምኅዳር፤ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ንግግር፤ የመንግስት ገቢ መጨመር እና የታክስ ከፋዩ እሮሮ፤ ሁለት የቱርኪዬ ዜጎች እና አንድ ኢትዮጵያዊ በታጣቂዎች መገደላቸው በኖሌ ካባ ወረዳ በግዲያና ዝርፍያ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው
    Más Menos
    28 m
  • የጥር 4 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    Jan 12 2026
    መጽሄተ ዜናችን አራት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ ያስደምጣል። የጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ወደ ጂቢቲ ጉዞ እና ወቅታዊ ሁኔታ ፣ በአዲሱ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃዉሞ እና የመንግስት ምላሽ ፤ በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን የምግብ እጥረት የፈጠረው መፈናቀል ፤ እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ክልሎች አዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎች መወለዳቸውን የተመለከቱ ዘገባዎች ይደመጣሉ።
    Más Menos
    19 m
  • የዜና መጽሔት፤ ጥር 1 ቀን 2018 አርብ
    26 m