Episodios

  • "የዳያስፖራ ባንክ አገልግሎት ክፍል ዓላማ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ፍላጎቶችና የባንኩን አቅርቦቶች በማያያዝ ለማገልገል ነው"አቶ ዘሪሁን ተከተል
    Mar 31 2026
    አቶ ዘሪሁን ተከተል፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ ባንክ ክፍል ሥራ አስኪያጅ፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት መካከል የተካሔደውን የመግባቢያ ሰነድ ፍረማ ፋይዳዎችን አንስተው ያስረዳሉ።
    Más Menos
    36 m
  • ኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ባዘጋጀችው የሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት ፎረም ከተለያዩ ኩባንያዎች ጋር የ13 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመች
    Mar 30 2026
    የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኅን ባለስልጣን በአንድ ዓመት ውስጥ ከማኅበራዊ ሚዲያዎች በናሙና ከታዩ 32 ሺህ ይዘቶች መካከል ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት የጥላቻና ሐሰተኛ መረጃዎች መሆናቸውን በጥናት መለየቱን አመለከተ
    Más Menos
    13 m
  • "የፊልም ኢንዱስትሪያችን ገና ዳዴ ማለት እንኳ አልጀመረም" ሶፎንያስ ታድሰ
    Mar 29 2026
    በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ፀሐፊ፣ አዘጋጅ፣ ዳይሬክተርና መምህር ሶፎኒያስ ታደሰ፤ የኢትዮጵያን የፊልም ኢንዱስትሪ የዕድገት ደረጃና የአሠራር ሂደቶች ነቅሶ ያመላክታል።
    Más Menos
    25 m
  • "በሚስጥር ከማኅበረሰቡ ውስጥ ተነቅለው የወጡ እውነቶችን የያዘ ነው፤ በሚስጥር ያደረግነው ነገር በአደባባይ ያስለቅሰናል ነው ፅንሰ ሃሳቡ" ሶፎኒያስ ታደሰ
    Mar 29 2026
    በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ፀሐፊ፣ አዘጋጅ፣ ዳይሬክተርና መምህር ሶፎኒያስ ታደሰ፤ በቅርቡ በአቦል ቴሌቪዥን ለታዳሚዎች ዓይነ ገብ ለመሆን የዕይታ መሰናዶው ስለተጠናቀቀለት ባለ 260 ክፍል ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ጭብጥ ቀንጭቦ ያጋራል።
    Más Menos
    Aún no se conoce
  • "ልጄ 'ማሚ እኔ ይኼን ቆዳዬን አልወደምው፤ ቀዪሪልኝ' ሲለኝ የተሰማኝን ስሜት በቃል ለመግለፅ ይከብዳል። በጣም ነው የከፋኝ።" ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ
    Mar 26 2026
    ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ፤ በሀገር ቤት ጎሠኝነትን፣ በሀገረ አውስትራሊያ ዘረኝነትን እምቢኝ ያሉ፤ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በእጅጉ የኩራት ሞገስን የተላበሱ ናቸው። ልጃቸው ዕድሜው አምስት ዓመት ሊሞላ ደርሶ ሳለ የገጠመው የቀለም ልዩነት ያሳደረባቸውን ሥነ ልቦናዊ ሁከት እንደምን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ፈውስ ሆኗቸው ከእነ ልጃቸው እንደተቋቋሙት ይናገራሉ። ያም አስባብ ሆኗቸው "አድዋና ሜልበርን" ያሏትን የስንኝ ቋጠሮ ያስደምጣሉ።
    Más Menos
    23 m
  • "ጠብን፣ መቀየምን ትፈራለች፤ ፍቅርን፣ ሰው ማክበርን ትወዳለች። በእምነቷም፣ በልጆቿም በትዳሯም ጠንካራ ነበረች።" የወ/ሮ ወርቅነሽ ባለቤት አቶ አብርሃም ተዘራ ገሠሠ
    Mar 26 2026
    ወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) ለሶስት ዓመታት ከማኅፀን ካንሰር ጋር ያካሔዱት ፍልሚያ አክትሞ ከእዚህ ዓለም በሕልፈተ ሕይወት ተለይተዋል። ባለቤታቸው አቶ አብርሃም ተዘራ፣ የቤተሰባቸው ወዳጅ አቶ ፍቅሬ (ራያ) ረታ እና የንስሃ አባታቸው መልአከ ፅዮን ቀሲስ እንግዳ ችሩ፤ የሜልበርን መካነ ሰላም ልደታ ለማርያም ወገብርኤል አስተዳዳሪ፤ የወ/ሮ ወርቅነሽን የሕይወት ዘመን አንስተው፤ ጥልቅ ሐዘናቸውን በመግለፅ ይዘክራሉ። የወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ ማርች 28 ቀን 2026 / መጋቢት 19 ቀን 2018 በወረቢ ቤተ መቃብር Corner Cemetery Rd & Railway Avenue 10:00 am ይፈፀማል።
    Más Menos
    17 m
  • ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ‘በጣም ትልቅ ስጦታ ሰጠችኝ‘ አሉ
    Mar 25 2026
    የግሪንስ ፓርቲ አውስትራሊያ ያለ ፓርላማ ይሁንታ ወደ ጦርነት እንዳትገባ የሚደነግግ ሕግ እንዲኖራት ፓርቲያቸው ዳግም መጠየቁን አስታወቁ
    Más Menos
    7 m
  • ኢትዮጵያ በዓለም 5ኛዋ ግዙፍ አበባ ላኪ ሀገር ተባለች
    Mar 25 2026
    በኢትዮጵያ የዩናይድ ስቴትስ ኤምባሲ ኢትዮጵያውያን የንግድና ጉብኝት ቪዛ አመልካቾች እስከ 15 ሺህ ዶላር የሚደርስ የማስያዣ ገንዘብ እንዲያሲይዙ የሚጠይቀው አሠራር ከመጋቢት 24 ቀን 2018 ጀምሮ ግብር ላይ እንደሚውል አስታወቀ
    Más Menos
    9 m