Episodios

  • Thread of Identity: Fashion as Culture and Industry | CfCA Ethiopia #13
    Jan 2 2026
    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 13 የማንነት ክሮች - ፋሽን እንደ ባህል እና እንደ ኢንዱስትሪ እንግዳ፡ ማኅሌት ተክለ/ማርያም | አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ በክፍል 13 ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት ፤ አዝጋጅ ተሾመ ወንድሙ የሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ መስራች እና አዘጋጅ ከሆነችው ማኅሌት ተክለ/ማርያም ጋር ውይይት ያደርጋል፡፡ ይህ ክፍል የኢትዮጵያን ፋሽን እና የፈጠራ ኢንዱስትሪ እድገት፣ተግዳሮቶችን እና መፃኢ እጣ ፈንታን ይቃኛል፡፡ ማኅሌት ከውጭ አገራት እስከ አገር ውስጥ የዘለቀ ጉዞዋን፣ በአፍሪካ ውስጥ እስከ አሁን ድረስ የዘለቀ የፋሽን መድረክን ስለመገንባቷ በተጨማሪም ስለማንነት፣ባህል እና ለፋሽን ኢንዱስትሪው ስላሉ እድሎች በውይይቱ ላይ ታጋራለች፡፡ በውይይቱ ላይ የሚነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች • ፋሽን እንደ የባህል እና የእለት ተእለት መገለጫ በኢትዮጵያ • የኢትዮጵያ እና አፍሪካ ፋሽን ኢንዱስትሪዎች እድገት • ዲዛይነሮች የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች፡ የማምረት ሂደት፣ቁሳቁሶች፣ፖሊሲ፣ በብዛት ማምረት • ፋሽን ዊክ ለፋሽን የመሟገቻ፣ለቱሪስት መስኅብነት እና ለስራ ፈጠራ መድረክ ሆኖ የማገልገል አቅሙ • "በኢትዮጵያ የመተረተ'' ፤ ሰዎች በአገራቸው ምርት እንዲኮሩ ማድረግ • ዘላቂነት፣ ለአካባቢ የሚስማማ፣ ለህዝብ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ የሚሸጥ እንዲሁም ባህልን የሚያከብር ፋሽን • በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ የፋሽን ገበያዎች የኢትዮጵያ ስፍራ ይህ ክፍል በፈጠራ ስራ ላይ ለተሰማሩ፣ለፖሊሲ አውጪዎች፣ለስራ ፈጣሪዎች፣ለተማሪዎች እንዲሁም በአፍሪካ በባህል ላይ ለተመሰረተ እድገት በሙሉ ፍላጎት ያላቸው ሁሉ ሊመለከቱት የሚገባ ነው፡፡ ይመልከቱ፣ያድምጡ እንዲሁም ውይይቱን ይቀላቀሉ፡፡ በባህል፣በፖሊሲ እና በአፍሪካ የፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ የሚያጠነጥኑ ተጨማሪ ውይይቶችን ለመከታተል ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡ Title: Thread of Identity: Fashion as Culture and Industry Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast | Episode 13 Guest: Mahlet T/Mariam | Host: Teshome Wondimu In Episode 13 of Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast, host Teshome Wondimu sits down with Mahlet Teklemariam (Mahlet T/Mariam), founder and organizer of Hub of Africa Fashion Week, Addis Ababa. This episode explores the growth, challenges, and future of Ethiopia's fashion and creative industries. Mahlet shares her journey from the Ethiopian diaspora to building one of Africa's most consistent fashion platforms, and discusses fashion as identity, culture, industry, and opportunity. Key topics include: • Fashion as cultural identity and everyday life in Ethiopia • The growth of Ethiopian and African fashion industries • Challenges designers face: production, materials, policy, and scale • Fashion weeks as platforms for advocacy, tourism, and job creation • "Made in Ethiopia" and building pride in local products • Sustainability, ethical fashion, and environmental responsibility • Ethiopia's place in African and global fashion markets This episode is a must-watch for creatives, policymakers, entrepreneurs, students, and anyone interested in culture-led development in Africa. Watch, listen, and join the conversation. Subscribe for more conversations on culture, policy, and creative industries in Africa.
    Más Menos
    57 m
  • The Canvas Speaks: Visual and Fine Arts in Ethiopia | CfCA Ethiopia #12
    Dec 12 2025

    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት፤ ክፍል 12

    ''ሸራ ይናገራል፤ የእይታ ጥበባት እና ሥነ-ጥበብ በኢትዮጵያ''

    እንግዳ፡ የእይታ ጥበባት አርቲስት፣ ገጣሚ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር፤ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን

    በዚህ አነቃቂና አይን ከፋች ክፍል፣ የኢትዮጵያን የእይታ ሥነ-ጥበባት እና የሥነ-ሥዕል ጥበብ ዘርፍ ጥልቀታቸውን፣ታሪካቸውን እና ተግዳሮታቸውን እንዳስሳለን፡፡

    እንግዳችን ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን በሥነ-ጥበብ እና በሙዚየም ስራ ውስጥ ለበርካታ አስርት ዓመታት እንደ የፈጠራ ሰራተኛ፣መምህር እና መሪ በመሆን ያገለገሉበትን ልምድ ይዘው የቀረቡ ሲሆን በጋራ በመሆን የሚከተሉትን ጉዳዮች እንወያያለን፡፡

    · በኢትዮጵያ የባህል ሥነ-ምህዳር ወስጥ የጎደለውን መሰረተ ልማት

    · ሙዚየሞች ለምን ከማከማቻ ስፍራነት ባለፈ ማደግ እንዳለበቸው

    · የመሰነድ፣የትችት እና የምርምር ጠቃሚነት

    · ማኅበረሰቦች ኪነ-ጥበባዊን ችሎታ እንዴት ተንከባክበው ማሳደግ እንደሚችሉ

    · የመንግስት ፖሊሲ፣ኢንቨስትመንት እና አህጉራዊ ትስስሮች ሚና

    · ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ የፈጠራ ትስስሮችን እንዴት እንደምትገነባ

    ሰብስክራይብ በማድረግ ወደ ፊት የሚወጡ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ክፍሎችን ይከታተሉ፡፡

    ከታች ኮሜንት በማድረግ ውይይቱን ይቀላቀሉ!

    Connect for Culture Africa Ethiopia Podcast– Episode 12
    🎨 The Canvas Speaks: Visual and Fine Arts in Ethiopia
    Guest: Bekele Mekonnen – Visual Artist, Poet, and Professor at AAU Ale School of Fine Arts and Design

    In this inspiring and eye-opening episode, we explore the depth, history, challenges, and untapped opportunities of Ethiopia's visual and fine arts sector.

    Our guest, Bekele Mekonnen, brings decades of experience as a creator, educator, and leader in fine arts and museum practice. Together we discuss:

    • The missing infrastructure within Ethiopia's cultural ecosystem
    • Why museums must evolve beyond storage spaces
    • The importance of documentation, critique, and research
    • How communities can nurture artistic talent
    • The role of government policy, investment, and continental networks
    • How Ethiopia can rebuild its creative connections within Africa

    Subscribe & stay updated on future episodes of Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast.
    Comment below and join the conversation!

    #1percentforculture #sustainablepublicfunding #EthiopianArt #FineArts #VisualArts

    Más Menos
    1 h y 5 m
  • Stages of Change: The Transformative Power of Theatre | CfCA Ethiopia #11
    Nov 21 2025
    ክፍል 11፡ የለውጥ መድረኮች: የትያትር ኃይል ለዘላቂ ለውጥ እንግዳ፡ መዓዛ ወርቁ፤ ጸሐፊ ተውኔት አቅራቢ፡ ተሾመ ወንድሙ በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ከዝነኛዋ ጸሐፊ ተውኔት መዓዛ ወርቁ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የባህል ተረክ ውስጥ ትያትር የተጫወተውንና እየተጫወተ ያለውን ከፍተኛ ሚና እንዳስሳለን፡፡ በትምህርት ቤቶች እና ሆቴሎች ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፤ሀገርን ለአንድ ዓላማ እስከማስተባበር ድረስ፣መዓዛ የኢትዮጵያ ትያትር አስደማሚ ጉዞን ታስቃኘናለች፡፡ በተጨማሪም ትያትር ለፊልም፣ቴሌቪዥን፣ትምህርት፣የሀገር ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ እንዲሁም የጋራ ማንነትን በመቅረጽ ረገድ ያለውን አስተዋጽኦ ጸሐፊ ወደ ኋላ በመመለስ ትዳስሳለች፡፡ በዚህ ክፍል የሚከተሉትን እናነሳለን • የኢትዮጵያ ትያትር ጥልቅ ታሪክ • ትያትር በኢትዮጵያ ፊልም እና ቴሌቪዥን ላይ የሚሳተፉ ባለተሰጥኦዎችን እንዴት ኮትኩቶ እንዳሳደገ • ኪነ-ጥበብ ለህብረተሰብ እድገት እና ውይይት ለምን አስፈላጊ እንደሆነ • የፖሊሲ፣የገንዘብ ድጋፍ እና ውይይት ከፍተኛ አስፈላጊነት • የትያትር መጻኢ እጣ ፈንታ በኢትዮጵያ እና አፍሪካ ይህ ለአርቲስቶች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ተማሪዎች እንዲሁም በባህል የለውጥ ኃይል ለሚያምኑ ሁሉ ጥልቀት ያለው ምልከታን የሚሰጥ እንዲሁም ወቅታዊ ውይይት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የፈጠራ እና የባህላዊ ኢንዱስትሪ ላይ ተጨማሪ ውይይቶችን ለመከታተል ሰብስክራይብ ያድርጉን እንዲሁም አዲስ ክፍሎች እንዳያመልጥዎት የደወል ምልክቱን ይጫኑ! Episode 11: "Stages of Change: The Transformative Power of Theatre" Guest: Meaza Worku (Playwright) Host: Teshome Wondimu In this episode of the Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast, we sit down with acclaimed playwright Meaza Worku to explore the powerful role theatre has played—and continues to play—in Ethiopia's cultural narrative. From its early beginnings in schools and hotels to its role in national mobilization, Meaza takes us through the remarkable journey of Ethiopian theatre. She reflects on its contribution to film, TV, education, nation-building, and the shaping of collective identity. We discuss: • The deep-rooted history of Ethiopian theatre • How theatre cultivated Ethiopia's film and TV talent • Why art is essential for societal growth and dialogue • The crucial need for policy, funding, and private-sector support • The future of theatre in Ethiopia and Africa This is an insightful and timely conversation for artists, policymakers, students, and anyone who believes in the transformative power of culture. Subscribe for more conversations on Ethiopia's creative and cultural industries. Don't forget to turn on notifications so you don't miss upcoming episodes! #1percentforculture #sustainablepublicfunding #ConnectForCultureAfrica #Theatre #CreativeIndustry
    Más Menos
    57 m
  • Learning the Arts: The Role of Education in Cultural Development | CfCA Ethiopia #10
    Oct 31 2025

    ጥበብና ትምህርት፡ በባህል ልማት ውስጥ የትምህርት ሚና |ክፍል 10|

    ወደ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት 10ኛ ክፍል እንኩዋን በደህና መጣችሁ!

    በዚህ ክፍል የሰላምና ሙዚቃዊ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር ተሾመ ወንድሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ምክትል ዲን/ኪዩሬተር፣ አርቲስት እንዲሁም ተመራማሪ ከሆኑት አገኘሁ አዳነ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ በመቅረጽ ረገድ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ያለውን ሚና ይዳስሳሉ፡፡

    የሚዳሰሱ ርዕሶች

    · የሥነ-ጥበብ ትምህርት ከስር መሰረት የመሰጠቱ ጥቅም
    · ለኢትዮጵያ ሥነ-ጥበብ የነበሩ ታሪካዊ እና ዘመናዊ አስተዋጽኦዎች
    · የሥነ-ጥበብ ስራዎችን ጠብቆ በማቆየት እና ሞያን በማሳደግ ረገድ ያሉ ተግዳሮቶች
    · ለአርቲስቶች፣ትምህርት ቤቶች እና ማኅበረሰቦች ያሉ እድሎች

    ይህ ክፍል ትምህርት እና ባህል በጋራ በመሆን እንዴት ብሩህ እና የሰለጠነ ህብረተሰብን እንደሚቀርጹ ለአርቲስቶች፣መምህራኖች እንዲሁም የባህል ወዳጆች እጅግ ጠቃሚ ምልከታን ይሰጣል፡፡

    ይህን ክፍል () እንዲሁም () ላይ በአማርኛ ማድመጥ ይችላሉ፡፡


    Welcome to Episode 10 of Connect for Culture Africa Ethiopia!

    In this episode, Teshome Wondimu sits down with Agegnehu Adane, Vice Dean at Addis Ababa University's Alle School of Fine Arts and Design, to explore the critical role of arts education in shaping Ethiopian society.

    Topics discussed include:

    The importance of grassroots arts education
    Historical and modern contributions to Ethiopian arts
    Challenges in archiving and professional development
    Opportunities for artists, schools, and communities
    Whether you're an artist, educator, or cultural enthusiast, this episode offers invaluable insights into how education and culture intersect to shape a vibrant, civilized society.

    #1percentforculture #sustainablepublicfunding #ArtsEducation #FineArts #ConnectForCulture

    Más Menos
    1 h y 18 m
  • Owning Creativity: The State of Copyright and IPR in Ethiopia | CfCA - Ethiopia #9
    Oct 10 2025

    ክፍል 9፡ የፈጠራ ባለቤትነት፡ የቅጂ እና የአእምሯዊ ንብረት መብት በኢትዮጵያ| ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት

    ይህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት በኢትዮጵያ የፈጠራ ዘርፍ ውስጥ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑትን የቅጂ መብት እና የአእምሯዊ ንብረት መብትን በጥልቀት ይዳስሳል፡፡

    የሚዳሰሱ ጉዳዮች

    · አሁን በሚገኙ ህጎች እና ረቂቅ ፖሊሲዎች መካከል ያለው ክፍተት
    · የበርን ኮንቬንሽን እና ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮሎች ጥቅም
    · የጋራ አስተዳደር ማኅበራት ሚና
    · ኢትዮጵያ ለምን አሁን ወደ ተግባር መግባት እንዳለባት
    · በዘርፉ የገንዘብ ድጋፍ፣ትምህርት እና ትብብር ጥቅም

    ይህን የባለሞያን ምልከታ የያዘውን ክፍል የፈጠራ ባለሞያዎች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ የባህል መሪዎች እና የአፍሪካ ባህል ተሟጋቾች ሊያዩት የሚገባ ነው፡፡

    ላይክ እና ሰብስክራይብ ማድረግ አይርሱ!

    This episode of Connect for Culture Africa Ethiopia Podcast dives into one of the most urgent issues in Ethiopia's creative sector: Copyright and Intellectual Property Rights.

    We explore:

    The gaps in current laws and draft policies
    The significance of the Berne Convention and international IP protocols
    The role of collective management societies
    Why Ethiopia needs to act now—not later
    The importance of funding, education, and unity in the sector
    Featuring expert insights from the sector's professional, this episode is a must-watch for creators, policy makers, cultural leaders, and advocates for African arts.

    Don't forget to like, share, and subscribe!

    #1percentforculture #sustainablepublicfunding #CreativeEconomy #BerneConvention #ConnectForCultureAfrica

    Youtube-link: https://youtu.be/4BL9xTqRskw

    Más Menos
    1 h y 3 m
  • Beyond the Spotlight: Circus as a Tool for Empowerment| Teklu Ashagir | CfCA - Ethiopia #8
    Sep 19 2025

    ከመድረክ ባሻገር፡ ሰርከስ እንደ አስቻይ የጥበብ ዘርፍ| ተክሉ አሻግር ከተሾመ ወንድሙ ጋር| ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት

    ሰላም ኢትዮጵያ ከኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ እንቅስቃሴ ጋር በጋራ ወደ ሚያቀርበው ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት እንኳን በደህና መጣችሁ፡፡

    በዚህ ክፍል ተሾመ ወንድሙ ከኢትዮጵያ ሰርከስ ብሔራዊ ማኅበር ፕሬዝደንት ከተክሉ አሻግር ጋር በመሆን ሰርከስ ያለምንም ተቋማዊ ድጋፍ ወይም መሰረተ-ልማት እንዴት ህይወትን እንደለወጠ፣ወጣቶችን እንዳበቃ እንዲሁም ኢትዮጵያ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ያላትን ዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እያደረገ እንደሚገኝ አይን ገላጭ ውይይት ያካሂዳሉ፡፡

    የሚዳሰሱ ርዕሶች

    · ኢትዮጵያ በሰርከስ ጥበብ ከዓለም አቀፍ መሪዎች መካከል የመሆኗ ሁኔታ

    · ከስር ጀምሮ እስከ ብቁ ባለሞያነት ድረስ ያለ ጉዞ

    · ሰርከስ እንደ ለውጥ እና ዲፕሎማሲ መሳሪያ

    · የሰርከስ ኢኮኖሚያዊ አንድምታ

    ይህ ውይይት ለፖሊሲ አውጪዎች፣ የፈጠራ ስራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች እንዲሁም ለህዝብ፤ የፈጠራ ኢንዱስትሪዎች ሀገራትን በመለወጥ ረገድ ያላቸውን ኃይል እንዲገነዘቡ ጥሪ የሚያቀርብ ነው፡፡

    ይመልከቱ እንዲሁም ኃሳብዎን ከስር ያጋሩ!

    ስለኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ እና 1% የብሔራዊ በጀትን ለባህል ስለማዋል እንቅስቃሴ ለመረዳት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡

    https://cfcafrica.org/

    ይህን ክፍል በስፖቲፋይ (Spotify) እና አፕል ፖድካስት (Apple podcast) ማድመጥ ይችላሉ፡፡

    Más Menos
    59 m
  • Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia - CfCA - Ethiopia #7
    Aug 29 2025

    የሀገር ገፆች፡ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ በኢትዮጵያ

    ክፍል 7 - ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት

    ደራሲ የዝና ወርቁ እና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችንና እድሎችን ይዳስሳሉ፡፡ የንባብ ልምድ ከማዳበር እስከ ፖሊሲ አስተዋጽኦ፣የህትመት ችግሮች፣ የቋንቋ ብዝኃነት እና ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን በመግለጽ ረገድ የዘርፉ መፃኢ እጣ ፈንታ በዚህ ውይይት ይነሳሉ፡፡

    የሚካተቱ ርዕሶች ዝርዝር

    ጸሀፊዎች በኅብረተሰብ ውስጥ ያላቸው ሚና
    በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ውስጥ የኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ
    ለጸሀፊዎች የመሰረተ-ልማት እና ድጋፍ ያለበት ሁኔታ
    ንባብን እንዲሁም መጻፍን ለማበረታታት መደረግ ስላለባቸው የማበረታቻ ስራዎች
    ትምህርት፣ጥልቅ ስሜት እና ተሰጥኦ ያላቸው ግንኙነት
    ባህልን በመጽሐፍት አማካይነት ለትውልድ ማስተላለፍ እንዲሁም ፖሊሲ እና ህትመት ያለበት ሁኔታ

    ይመልከቱ፣ያጋሩ እንዲሁም የውይይቱ አካል ይሁኑ!

    ተጨማሪ የባህል፣ፈጠራ እና ማኅበረሰብ ላይ የተዘጋጁ የፖድካስት ይዘቶች እንዲደርስዎ ላይክ፣ኮሜንት እና ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡


    Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia

    Episode 7 – CfCA Ethiopia Podcast

    Featuring: Writer Yezina Worku with Teshome Wondimu

    In this powerful episode, we sit down with renowned Ethiopian writer Yezina Worku to explore the challenges and opportunities in the world of Ethiopian literature today.

    From cultivating a reading culture to the role of policy, publishing struggles, language diversity, and the future of storytelling in Ethiopia — this conversation dives deep into what it means to write our truths and build a literary future.

    Topics include:

    The writer's role in society
    The state of literature in different Ethiopian languages
    The lack of infrastructure and support for writers
    Efforts that need to be carried out to promote reading and writing
    The intersection of education, passion, and talent
    preservation of culture through books, the status of publishing and policy

    Watch, share, and be part of the conversation.

    Don't forget to like, comment, and subscribe for more content on culture, creativity, and community.

    #1percentforculture #sustainablepublicfunding

    Más Menos
    1 h y 7 m
  • Sounds of a Nation: The Ethiopian Music Scene - CfCA - Ethiopia #6
    Aug 8 2025

    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 6

    ርዕስ፡ የሀገር ድምፅ-የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወግ

    እንግዳ፡ ጆርጋ መስፍን - ሳክስፎኒስት፣ሙዚቃ አቀናባሪ

    አዘጋጅ፡ ተሾመ ወንድሙ - የሰላም እና ሙዚቃዊ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ

    በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት ክፍል የኢትዮጵያን ሙዚቃ ትሩፋት፣የአሁን ተግዳሮቶቹን እንዲሁም ለወደፊት ያለውን ከፍተኛ አቅም እንዳስሳለን፡፡

    እንግዳችን ጆርጋ መስፍን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ትሩፋት ላይ በማተኮር ከቅዱስ ያሬድ እስከ ዛሬ ዘመን የሚገኘው ወጣት መር ፈጠራን ይዳስሳል፡፡ ጆርጋ መስፍንና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን እንደ የኦሪጅናል ካሴቶች አለመኖር፣ተገቢ የክምችት ሁኔታ አለመኖር፣ጊዜ ያለፈባቸው ወይም ተደራሽ ያልሆኑ ኮንትራቶች እና ስለባህላዊ መሰረተ ልማት አስፈላጊነት ይዳስሳሉ፡፡

    የሚዳሰሱ ርዕሶች ዝርዝር

    · ሙዚቃን ጠብቆ የማቆየት ተግዳሮቶች እና የብሔራዊ ክምትቶች መጥፋት
    · በሙዚቃ ኮንትራቶች እና በቅጂ መብት ጥበቃ የሚያስፈልጉ የህግ መሻሻሎች
    · በወጣቶች የሚመራ ህዳሴ እና እንደ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ያሉ ተቋማት ጠቃሚነት
    · በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ቱር ማድረግ
    · የኢትዮጵያ ሙዚቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ እንዲሆን ለምን ወጥነቱን መጠበቅ እንዳለበት
    · የባህል ዘርፉን የሚገነቡ እንጂ የማያፍኑ ፖሊሲዎችን መገንባት

    ይህ ክፍል ፖሊሲ አውጪዎች፣አርቲስቶች፣አስተማሪዎች እና የባህል መሪዎች የኢትዮጵያን ልዩ የሙዚቃ ድምጸት ጠብቀው እንዲያቆዩ እና እንዲለውጡ ጥሪ የሚያቀርብ ነው፡፡


    🎙️ Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast | Episode 6
    Title: "Sounds of a Nation: The Ethiopian Music Scene"
    👤 Guest: Jorga Mesfin – Saxophonist, Composer
    🎤 Host: Teshome Wondimu – Founder & Executive Director, Selam

    In this powerful episode of Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast, we explore the state of Ethiopian music—its legacy, its current struggles, and its immense future potential.

    Our guest, Jorga Mesfin, reflects on the rich musical heritage of Ethiopia, from the time of Saint Yared to today's youth-led innovation. Together with host Teshome Wondimu, they unpack urgent issues: the loss of original cassettes, the lack of proper archiving, outdated or inaccessible music contracts, and the need for strong cultural infrastructure.

    🎶 Topics discussed include:

    The crisis of music preservation and the loss of national archives
    Legal reforms needed in music contracts and copyright protection
    Youth-driven revival and the importance of institutions like Yared Music School
    Touring locally vs. internationally
    Why Ethiopian music should maintain its authenticity for global success
    Building policies that support—not stifle—the cultural sector
    This episode is a call to action for policymakers, artists, educators, and cultural leaders to unite in preserving and evolving Ethiopia's sonic identity.

    Más Menos
    1 h y 27 m
adbl_web_global_use_to_activate_DT_webcro_1694_expandible_banner_T1