የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ Podcast Por SBS arte de portada

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

De: SBS
Escúchala gratis

Acerca de esta escucha

ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።Copyright 2025, Special Broadcasting Services Ciencias Sociales
Episodios
  • "ኢትዮጵያውያን መጥተው ድጋፋቸውን ቢቸሩኝ ደስ ይለኛል" ሶሊያና እርሴ
    Apr 3 2025
    አንፀባራቂ ኮከብ በመሆን ላይ ያለችው ሶሊያና እርሴ፤ ከትውልድ ከተማዋ ጎንደር፣ ከዕድገት ክፍለ ሀገሯ ትግራይ ተነስታ፤ እንደምን ትንፋሽን የሚያስውጥ፣ የልብ ትርታን ከፍና ዝቅ የሚያደርግ፣ ምትሃታዊ እንጂ ከቶውንም የመድረክ ዕውነታ የማይመስለው፤ ግና ሞገስን የተላበሰ አካላዊ መተጣጠፍ ኮንቶርሽን ተጠባቢ ለመሆን እንደበቃች ታወጋለች። ከኤፕሪል 3 እስከ ሜይ 11 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከ Club Kabarett ጋር በመሆን ለሕዝብ ስለምታቀርበው ዝግጅቷ ታነሳለች። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም በሥፍራው እንዲገኙ ትጋብዛለች።
    Más Menos
    9 m
  • "የትም ሀገር ብንሆን ኢትዮጵያን ከውስጣችን ማውጣት አይቻልም፤በአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው የሰርከስ ማዕከል ግንባታ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ቢሆኑ ደስ ይለኛል"ሶስና ወጋየሁ
    Jan 29 2025
    የቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ ከግለ ሕይወት ታሪካቸው ጋር አሰናስለው እንደምን ከሀገረ አውስትራሊያ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ፤ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆነውን የሰርከስ ማዕከል በእንጦጦ ፓርክ በመገንባት ላይ እንዳሉ ይናገራሉ።
    Más Menos
    22 m
  • ሶስና ወጋየሁ፤ ከአውስትራሊያ ጥገኝነት ጥየቃ ለክብር ሽልማት መብቃት
    Jan 21 2025
    የቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ እንደምን በሀገረ አውስትራሊያ ከጥገኝነት ጥየቃ ለከፍተኛ የክብር ሽልማት እንደበቁ ያወጋሉ።
    Más Menos
    14 m
adbl_web_global_use_to_activate_T1_webcro805_stickypopup
Todavía no hay opiniones