Radio D | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle Podcast Por DW.COM | Deutsche Welle arte de portada

Radio D | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

Radio D | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

De: DW.COM | Deutsche Welle
Escúchala gratis

OFERTA POR TIEMPO LIMITADO | Obtén 3 meses por US$0.99 al mes

$14.95/mes despues- se aplican términos.
ፓውላና ፊሊፕ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮችን ይመረምራሉ። ጋዜጠኞቹ በመላው ጀርመን በሚያደርጉት ጉዞ በማጀብ የጀርመንኛ ቋንቋን ይማሩ! ይኸው የትምህርት ክፍል በተለይ አድምጦ የመረዳት ችሎታን ያዳብራል።2024 DW.COM, Deutsche Welle Aprendizaje de Idiomas
Episodios
  • ክፍል 26 - የአይሀን ስንብት
    Sep 22 2009
    የሚያሳዝን ዜና ፦ ባልደረባ አይሀን ወደ ቱርክ ስለሚሄድ ይሰናበታል። ምንም እንኳን የተቀሩት ባልደረቦች ለስንብቱ ስጦታ ቢያዘጋጁም ተደስተው ማክበር ግን አልቻሉም። ፓውላ ጠዋት ወደ ቢሮ እንደመጣች ወዲያው ፓርቲ ማዘጋጀት አለባት። የፓርቲው ምክንያት ግን አላስደሰታትም። አይሀን የ Radio D ዝግጅት ክፍልን ለቆ ወደ ቱርክ አባቱን ለመርዳት ይሄዳል። በስንብቱ ላይም አጭር ንግግርና ጓደኛውን ኡላሊያ የሚያስታውስበት ስጦታ ለአይሀን ይሰጡታል። ለበዐሉ ስንብት ሲሉ ፕሮፌሰሩ በዚህ ምዕራፍ ስለ ሰዋሰው አይመለከቱም። ሆኖም የተወሰነ ነገሮች እንዴት ዋና ቃላቶች እንደሚዋኀዱ ከማለት ወደ ኋላ አይሉም።
    Más Menos
    15 m
  • ክፍል 25 - የመርከቦች ሰላምታ
    Sep 22 2009
    ጋዜጠኞቹ "getürkt" የሚለውን ቃል ትርጉም እያፈላለጉ ነው። በተጨማሪም አስገራሚ የሆነ ወደብ ይጎበኛሉ። እዛም እያንዳንዱ መርከብ በተለየ ሁኔታ ሰላምታ ይሰጠዋል።ቪልኮም ሆፍት በተባለው ወደብ እያንዳንዱ መርከብ በክፍለ ሀገሩ ብሔራዊ መዝሙር ሰላምታ ይሰጠዋል። የክፍለ ሀገራቸውን ባንዲራ እያውለበለቡ ይሄዳሉ። በአንድ የማድመጥ ትምህርት ላይ ፊሊፕና ፓውላ የዚህን የስራ ዘርፍ በትክክል ይመለከታሉ። "getürkt" የሚለው ቃል ትርጉምም ከዚህ ስራ ጋር ይገነኛል። የዝግጅት ክፍል ደግሞ አይሀን የረፍት ጊዜውን ስለ ጉጉቶች መፅሀፍ በማንበብ ያሳልፋል። ኡሌሊያ ማንበብ ስለማትችል አይሀን ያነብላታል። ይህም ምዕራፍ የተሳቢ ግሶችን ይመለከታል። አንድ ግስስ እንዴት በተሳቢው አማካይነት ይቀየራል?
    Más Menos
    15 m
  • ክፍል 24 - የ ሀንቡርግ ጋዜጣ
    Sep 22 2009
    ጉጉት ኡላሊያ ጋዜጠኞቹን ወደ ትክክለኛው መስመር ትመራቸዋለች። እነሱም የሀንቡርግ ጋዜጣ አዘጋጆች እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀር ይደርሱበታል። ፊሊፕ የሚያደርገውም አስተያየት ፓውላ ትደነግጣለች። የሀንቡርግ ጋዜጣ አዘጋጆች አውቀው ባህር ዳር ታየ የተባለውን የአሳ ነባሪ ታሪክ ፈጥረው እንደፃፉ ፓውላ ፣ ፊሊፕና ኡላሊያ ይደርሱበታል። ይህንንም ያደረጉት የአንባቢያቸውን ቁጥር ለመጨመር ሲሉ ነው። በኋላም ፊሊፕና ፓውላ በሆነ በአንድ ቃል አጠቃቀም ይጣላሉ። ፊሊፕም ፓውላ እንድትረጋጋ ሲል የወደቡ እንኳን ደህና መጡ መቀበያ ጋር ይጋብዛታል። ፊሊፕ ለሚለው ነገር ተጠንቅቆ ቢሆን ኖሮ ፓውላን ባላስቆጣት ነበር። በተረፈ የሚነጠሉ ግሶችን እናያለን። አንዳንድ የግስ ተሳቢዎች የግሱን ትርጉም የበለጠ ያብራራሉ። አልፎ አልፎም ግሱን ከተሳቢው ነጥሎ በቅድመ ቃል መልክ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ምዕራፉ ይመለከታል።
    Más Menos
    15 m
Todavía no hay opiniones